የዮሐንስ ወንጌል ተከታታይ ጥናት

ከእግዚአብሔር ጋር ይበልጥ እንደትተዋወቁ ብሎም በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ እድገት እንድትቀጥሉ ተከታታይ የኢሜይል ትምህርት ነው። ትምህርቱ የዮሐንስ ወንጌል መፅሐፍ ላይ ሲሆን ይህ ትምህርት የተወሰደው ከአጋር አገልግሎታችን እንግሊዘኛ ድህረ ገፅ www.startingwithgod.com ከሚለው ከኢንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም ነው።

ሰላም

ይህን የመንፈሳዊ ሕይወት ጅማሬ ተከታታይ ትምህርት ለመካፈል ፈቃደኛ በመሆናችሁ ደስ ብሎኛል። ይህ አሁን የምልክላችሁ በጣም ጠቃሚ ትምህርት ነው፣ ምክንያቱም ይህ ትምህርት እግዚአብሔርን በደንብ እንድታውቁት ስለሚያደርጋችሁ። የዮሐንስ ወንጌል ስለ እግዚአብሔር በርካታ እውነቶችን በውስጡ አዝሏል ደግሞም ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንዴት ልትመለከቱት እንደሚገባ ያሳያል። በሁለት ምክንያቶች፣ የዮሐንስን ወንጌል ከእኔ ጋር አብራችሁ እንደታጠኑ እጋብዛችኃለው፡

  • 1ኛ፡ ኢየሱስን በደንብ እንድታውቁት፡፡
  • 2ኛ፡ ለቀሪው ዘመናችሁ መጽሐፍ ቅዱስህን በግል እንዴት ማጥናት እንደምትችሉ እንደምሳሌ ለማሳየት፡፡

ምላሽ የሚጠበቅበት የቤት ሥራ የለበትም ምንም ተጨማሪ ነገርም አንጠይቅም። በዮሐንስ ውስጥ የሚገኙትን ዋና ዋና ነጥቦች እንጂ ሙሉ ጥቅሶቹን በጠቅላላ አንሸፍንም። እደተለመደው፣ በማንኛውም ጊዜ ደግሞ ማቋረጥ ይቻላል። ምርጫው በሁሉም ኢሜይሎች ግርጌ መጨረሻ ላይ ይቀመጣል።

እያንዳንዱ ኢሜል ከእግዚአብሔር ጋር ያለችሁን ህብረት እንድትረዱና እንድታውቁ ይረዳችኋል። የሚቀጥለውን ፎርም በመሙላት የመጀመሪያውን ኢሜይል በጥቂት ደቂቃ ታገኛላችሁ።

ጥያቄ አለዎት?

ጥያቄዎትን ልንመልስ እንፈልጋለን:: አብሮን በሚሰራው ድረ-ገጽ (habeshastudent.com) ላይ ያለን የኢሜይል ፎርም ነው የምንጠቀመው::

Copyright © 2024. Made by Great Commission Ministry Ethiopia.